St. Kidane-Mehret and Archangel St. Gabriel St. Kidane-Mehret and Archangel St. Gabriel

ቅድስት ኪዳነ ምህረት ወቅዱስ ገብርኤል

በኦስትሪያ ቬና ሐመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ወቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

ቪዲዮዎች

የበፊት ቀጥታ ስርጭቶች - ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን

አገልግሎቶች

ይህም ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጅ ሌላ አይደለም ይህም የሰማይ ደጅ ነው።

Service Icon

ሥርዓተ ቅዳሴ

ቅዳሴ ማለት “ቀደሰ፣ ባረከ፣ አመሰገነ፣ አከበረ፣ ማለት ሲሆን የቃሉም ትርጉም መቀደስ- መባረክ ማመስገን ማለት ነው:: ሥርዓተ ቅዳሴ የሚለውን በአንድ ትንፋሽ አንብበን ስንተረጉመው : የምስጋና መርሐ ግብር (የምስጋና ሥርዓት) ማለት ይሆናል።

ቅዳሴ የተጀመረው በመላእክት ነው። መላእክት መፈጠራቸው ለምስጋና እንደመሆኑ መጠን ፤ መላእክት ሲፈጠሩ ምስጋና/ቅዳሴ/ ተሰጥቷቸዋል። ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ፭ቱ ምሥዋዕቶች ተሞልተው ይገኙበታል እዚህንም ፭ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡

Service Icon

ምሥጢረ ቁረባን

ምስጢረ ቁርባን ከአምስቱ አዕማደ ምስጢራት አንዱ ነው፡፡ ሃይማኖታቸው የቀናና እውነተኛ የሃይማኖትን መንገድ ያቀኑ ቀደምት አበው (ሠለስቱ ምዕት) “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት (ከሁሉ በላይ በምትሆን የሐዋርያት ጉባዔ በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን)” ብለው የሃይማኖትን ድንጋጌ ያስቀመጡት በቅድስት ቤተክርስቲያን ምስጢረ ምስጢራት (የምሥጢራት ሁሉ ማጽኛ ማኅተም) የተባለው ምስጢረ ቁርባን ስለሚፈጸምባት ነው፡፡

Service Icon

ሰንበት ት/ቤት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ማለት የመንፈሳዊ ሕይወታቸው መሪ ብቻ ሳትሆን የባህል፣ማንነት እና ስነልቦናዊ ፋይዳ ሁሉ የሚገለጥባት ልዩ አካሉ ነች። ስለሆነም ወጣቱን ትውልድ ወደ መልካም የኑሮ ደረጃ ለማድረስ ከተፈለገ ከሁሉ አስቀድሞ የማንበብ እና የመጻፍ ችሎታ እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ከወላጅ ቤተሰብ የሚጠበቅ ቢሆንም ወጣቱን ትውልድ በተጨማሪ በእውቀት የታገዘ እና መልካም ስነ ምግባርን የተከተለ አስተዳደጋቸውን የሚከታተሉ የእምነት ተቋማት ማደራጀት እና ማሳደግ ወሳኝ ጉዳይ ነው።

Service Icon

ጥምቀት / ጋብቻ

ምስጢረ ጥምቀት ፦ በምስጢራዊ (በሃይማኖታዊ) ፍቺው በተጸለየበት ውሃ (ማየ ኅይወት) ውስጥ በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ብሎ የመውጣት ሂደት ነው (ማቴ 28፡19)። ጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ተወልደን የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት (ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና) ምሥጢር ነው።
ሥርዓተ ተክሊል ፦ ጋብቻቸዉን የሚፈጽሙ ምእመናን እስከ ሞት ድረስ ላይለያዩ በፍጹም ፍቅር ይዋሓዳሉ፡፡ ሽንገላና ግብዝነት በሌለበት እውነተኛ ፍቅር ይጣመራሉ፡፡ እግዚአብሔርን የሚፈሩና ወላጆቻቸውን የሚያከብሩ ልጆችንም ያፈራሉ፡፡ ጥንዶቹ የመከባበርና የመፈቃቀር፣ የመረዳዳትና የመተማመን፣ የመስማማትና የመተማመን ጸጋ ይታደላሉ፡፡

Service Icon

ንስሐ / ጸሎት

ንስሐ ፦ ነስሐ ተፀፀተ ካለው የተገኘ ሲሆን ፤ ንስሐ ማለት በሠሩት ኃጢአት መፀፀት ፣ ማዘን ፣ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ መወሰን ማለት ነው። ንስሐ ከዘለዓለማዊ ፍርድ የሚያድን ፤ ዘማዊውን እንደ ድንግል ፤ ሌባውን መጽዋች የሚያደርግ በፊት ከተሠራው ኃጢአት ንጹህ አድርጎ ፤ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሚያደርግ ምሥጢር ነው ።
ሥርዓተ ጸሎት ፦ ክርስቲያን ሥርዓት ጸሎት በሦስት ይከፈላል፤ የግል ጸሎት፣ የማኅበር ጸሎት፣ የቤተ ሰብ ጸሎት በመባል ይታወቃል፤ እያንዳንዱ ክርስቲያን የሚጸልየው ጸሎት የግል ጸሎት ሲባል በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚጸለየው የሚደርሰው ምስጋና፣ ሰዓታቱ ጸሎት፣ የማኅሌቱ፣ የጸሎተ ቅዳሴው፣ ምህላው ጸሎት የኅብረት ጸሎት ይባላል፤ ሌላው ደግሞ በቤተ ሰብ ውስጥ የሚደረገው ጸሎት ደግሞ የቤተ ሰብ ጸሎት ይባላል፡፡

Service Icon

ክርስትና / ፍትሐት

ክርስትና ፦ ልንነሣ ስንመጣ ደግሞ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የማይጠፋ ስምን ትሰጠናለች፡፡ በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት ስንፈልግ የምንጠራው ቤተ ክርስቲያን በሰጠችን የክርስትና ስም ነው፡፡ የክርስትና ስም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊት ያለው ነው፡፡
ፍትሐት ፦ ማለት ከዚህ ዓለም በሞት ለሚለዩ ሰዎች በሕይወተ ሥጋ ሳሉ ከሠሩትና ከፈጸሙት በደል እንዲነጹ ከማእሠረ ኃጢአት እንዲፈቱ ወደ እግዚአብሔር የሚቀብ ጸሎት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለሙታን ጸሎተ ፍትሐት እንዲደረግ ታዝዛለች፡፡

ቤተሰብ ይሁኑ

ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ፡፡

ዘወትር እሁድ:

6:30 AM
ክርስትና ማንሳት
7:30 AM
ጸሎተ ኪዳን
8:00 AM
ሥርዓተ ቅዳሴ በበዓልት ቀን 7:30 ላይ ይጀምራል
10:30 AM
መዝሙር እና ትምህርተ ወንጌል በበዓልት ቀናት ታቦት ይወጣል
11:30 AM
ጠበል ጻዲቅ
12:00 AM
ሰንበት ት/ቤት (ልጆች 4–11 ዓመት)
12:30 PM
ሰንበት ት/ቤት (ልጆች 12+ ዓመት)
Church Location Map

አድራሻ:
Pfarrplatz. 3, 1190 Vienna, Austria



አቅጣጫ:
ቤተክርስቲያኑ በህዝብ ትራንስፖርት በቀላሉ ማግኘት ይቻላል.
አውቶብስ: በአውቶቡስ ቁ. 38A ከሃይሊገንስታድት ወደ Himmelstraße ይሂዱ እና "Fernsprechamt Heiligenstadt" ማቆሚያ ላይ ይውረዱ።
200ሜ ይራመዱ ወደ ቀኝ ይታጠፉ እና 200ሜ ይራመዱ።
መኪና፡ የመኪና ማቆሚያ በአቅራቢያ ባሉ መንገዶች ላይ ይገኛል።

በጎግል ካርታ ላዝ ክፈት

ስለ ቤተክርስትያናችን

ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት ጻድቃን ወደ እርሷ ይገባሉ።
(መዝ. 117 ቁ. 20)

showcase

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በኦስትሪያ የደብረ ሲና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በኦስትርያ እና አካባቢው ለሚኖሩ ለተዋህዶ ቤተሰቦች ለሁለት አሥርት ዓመታት ያህል መንፈሳዊ አገልግሎት ስትሰጥ ኖራለች አሁንም እያገለገለች ትገኛለች።

ቤተ ክርስቲያኗ ዘወትር እሁድ ማለዳ ፀሎተ ኪዳን ፣ ጥምቀተ ክርስትና ፣ ስርዓተ ተክሊል ፣ ፀሎተ ቅዳሴ ፣ ትምህርተ ንሰሓ ፣ ፀሎተ ፍታት እንዲሁም የሰብከተ ወንጌል እና የመንፈሳዊ መዝሙር አገልግሎት በመሰጠት በዙሪያዋ ለአሉ የክርስቶስ ቤተሰቦች የመንፈስ ምግብ እና ለሀይማኖታቸው ብርታት ሆና እያገለገለች ትገኛለች።

በሥሯ ባሉ እግዚሃብሔር ለአገልግሎት በፈቀደላቸው ወንድሞች እና እህቶች ብርታት ቤተ ክርስቲያኗ በየግዜው የሚከበሩ የቤተ ክርስቲያን ቅዱስ በዓላትን በመዘከር እና በማክበር የክርስቲያን ቤተሰቦች ከበረከቷ እንዲካፈሉ ታደርጋለች። በቋሚነትም ብርሃነ ልደቱን ፣ ብርሃነ ጥምቀቱን ፣ ብርሃነ ትንሳኤ ፣ ውብርሃነ መስቀሉን ፣ የታህሳስ እና የሐምሌ ገብርኤል ፣ የየካቲት እና የነሐሴ ኪዳነ ምሕረትን እና ሌሎችንም ዓመታዊ ክብረ በዓላትን ታከብራለች። ቤተ ክርስቲያናችን እርሶ እና ቤተሰብዎ የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ሁል ግዜም ጥሪዋን ታስተላልፋለች። ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ እና ማህበራዊ አገልግሎት ሆነ ለተጨማሪም መረጃ ድህረ-ገፃችን በመጎብኘት መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።

የቤተ-ክርስቲያናችን አመሰራረትና ታሪክ

ከዛሬ ሰላሳ ዓመት በፊት በኦስትሪያ ላይ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አልተቋቋመም ነበር። በሀገሪቷ ውስጥም ይኖሩ የነበሩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተሰቦች ለሃይማኖታቸው የሚሆን መንፈሳዊ አገልግሎት ለማግኘት እጅግ ይቸገሩ ነበር። በዚህም የተነሳ የሃይማኖት ክብረ በዓላትንም ለማክበር በኦስትሪያ አቅራቢያ ወደ ሚገኙ ሀገራት አልፎ አልፎም ይጓዙ ነበር። ምዕመኑ ከሚጓዙባቸው ሀገራት መካከል ጀርመን አንዷ ስትሆን በኮለኝ ከተማ የሚገኘው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ተጠቃሽ ነው።

ካህናት እና ዲያቆናት

ቤተ-ክርስቲያናችንን ደከመኝ ሳይሉ የሚያገለግሉ ልጆችዋ

የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ

አባ ወልደ ዮሐንስ አጥናፉ

ቀሲስ

ቀሲስ ሚሊዮን ተስፋየ

ዲያቆን

ኖኤል

ዲያቆን

ኤልፊዎስ ደረጀ

አጽዋማት እና በዓላት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚከበሩ ዓበይት በዓላትና አጽዋማት

destination

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት

ታኅሣሥ ፳፱ ቀን

በዓለ ልደት፣ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እርቅ የተፈጸመበት በዓላችን ነው፡፡ ለሞት ከመገዛት የዳንበት፤ ጨለማው ተወግዶልን የብርሃን ልጆች የኾንበት፤ የእባብ ራስ የተቀጠቀጠበት፤ ከምድር ወደ ሰማይ ያረግንበትና ከመላእክት ጋር ኾነን ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀረብንበት፤ ከነቢያት ኅብረት ጋር አንድ የኾንበት በዓል ነው፡፡ ድንቅ የተዋሕዶ ምሥጢር የተፈጸመበትን ይህን ልዩ በዓል በመንፈሳዊ ሥርዓት ማክበር ይገባናል፡፡

destination

በዓለ ጥምቀት

ጥር ፩፩

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ለእኛ ለክርስቲያኖች የምትፈጽምልን የጥምቀት ሥርዓት ከክርስቶስ ጋር የሞቱም የትንሣኤውም ተካፋይ መሆናችንን የሚያስረዳ ነው። ምክንያቱም ተጠማቂው ከውኃ ውስጥ መግባቱ ከጌታ ጋር መሞቱን ያመለክታል።

destination

ስቅለት ዓርብ

ሚያዚያ ላይ

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡

destination

በዓለ ትንሣኤ

ሚያዚያ ላይ

ዓለም በጨለማ ተውጣና የሰው ዘር በሙሉ በኃጢአት ቁራኝነት ተይዞ የዲያብሎስ ባሪያ በነበረበት ዘመን ብርሃናተ ዓለም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ሞትን አጥፍቶ ብርሃንን ለገለጠበት ለትንሣኤው አድርሶናል ክብር ምስጋና ይገባዋል!!!

destination

የመስቀል በዓል

መስከረም ፲፯

በሀገራችን ኢትዮጵያ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀል የተለየ ክብር አለው፡፡ የሰውን ዘር በሙሉ ለማዳን ሲል ብዙ ጸዋትወ መከራ የተቀበለበትንና ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስ ያገኘንበት ግማደ መስቀሉ በዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ከእስክንድርያ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበትን የመታሰቢያ በዓል በየዓመቱ መስከረም ፲ ቀን እናከብረዋለን፡፡

destination

በዓለ ዕርገት

ነሐሴ ፩፮

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያረገችበት ዕለት ነሐሴ ዐሥራ ስድስት ቀን በቤተ ክርስቲያናችን ይከበራልና እኛም ስለዕርገቷ እንዲህ እንዘክራለን፤

ዜናዎች

ብሎግ እና አዲስ መረጃዎች